አብርሃምም ልጁን ይስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በወርቅም የገዛውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ። የሥጋቸውንም ቍልፈት እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ።
ዘፍጥረት 34:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከተማዪቱም በር የሚገቡ ሁሉ ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን እሺ አሉ፤ ወንዶችም ሁሉ የሰውነታቸውን ሸለፈት ተገረዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከከተማዪቱ በር ውጭ የተሰበሰቡት ሁሉ በኤሞርና በልጁ በሴኬም ሐሳብ ተስማሙ፤ በከተማዪቱም ያሉት ወንዶች ሁሉ ተገረዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማይቱም አደባባይ የሚወጡ ሁሉ ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን “እሺ” አሉ፥ ከከተማይቱ አደባባይ የሚወጡት ወንዶች ሁሉ ተገረዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተማይቱ ነዋሪዎች ሁሉ ሐሞርና ሴኬም ባቀረቡት ሐሳብ ተስማምተው ወንዶች ሁሉ ተገረዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማይቱም አደባባይ የሚወጡ ሁሉ ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን እሺ አሉ ከከተማይቱ አደባባይ የሚወጡት ወንዶች ሁሉ ተገረዙ። |
አብርሃምም ልጁን ይስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በወርቅም የገዛውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ። የሥጋቸውንም ቍልፈት እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ።
ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ የኬጢ ሰው ኤፍሮንም የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦
መንጋቸውም፥ የጋማ ከብቶቻቸውም፥ ገንዘባቸውም ሁሉ ለእኛ አይደሉምን? ነገር ግን በዚህ ብቻ ከመሰልናቸው ከእኛ ጋር ይቀመጣሉ።”