ዘፍጥረት 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም በዚያ ቀን ወደ ሴይር ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዔሳው በዚሁ ዕለት ወደ ሴይር ለመመለስ ተነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም በዚያኑ ቀን ወደ ሴይር መንገዱ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዔሳው በዚያኑ ቀን ጒዞውን በመጀመር ወደ ኤዶም ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳውም በዚያን ቀን ወደ ሴይር መንገዱን ተመለሰ። |
ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን?” አለ። እርሱም፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘቴ ይበቃኛል” አለ።
ያዕቆብ ግን በሰፈሩ አደረ፤ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ማኅደር ብሎ ጠራው።
የፍልስጥኤማውያን መሳፍንትም ወደ እርስዋ ወጥተው፥ “እርሱን አባብለሽ በእርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን” አሉአት።