ንጉሡም አሳ በይሁዳ ሁሉ ላይ አዋጅ ነገረ፤ ማንም ነጻ አልነበረም፥ ንጉሡ ባኦስም የሠራበትን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰደ፤ የይሁዳም ንጉሥ አሳ የብንያምንና የመሴፋን ኮረብታ ሠራበት።
ዘፍጥረት 31:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም አለው፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው እንለያያለንና ራእይን የገለጠልኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይመልከት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ምጽጳ ተባለ፤ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሏልና፤ “እኛ በተለያየን ጊዜ፣ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ታዛቢ ሆኖ ይቁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም “ምጽጳ”፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው በተለያየን ጊዜ ጌታ በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይጠብቅ” ብሏልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “እንግዲህ ከዚህ በምንለያይበት ጊዜ እግዚአብሔር እኔንና አንተን ይጠብቀን” በማለት ያንኑ ስፍራ ምጽጳ ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ በተለያየን ጊዜ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይጠብቅ ብሎአልና። |
ንጉሡም አሳ በይሁዳ ሁሉ ላይ አዋጅ ነገረ፤ ማንም ነጻ አልነበረም፥ ንጉሡ ባኦስም የሠራበትን የራማን ድንጋይና እንጨት ወሰደ፤ የይሁዳም ንጉሥ አሳ የብንያምንና የመሴፋን ኮረብታ ሠራበት።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
ዮፍታሔም ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም መስፍን ይሆናቸው ዘንድ በላያቸው አለቃ አድርገው ሾሙት፤ ዮፍታሔም ቃሉን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በመሴፋ ተናገረ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ።