Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 31:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 ደግሞም “ምጽጳ”፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው በተለያየን ጊዜ ጌታ በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይጠብቅ” ብሏልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 ደግሞም ምጽጳ ተባለ፤ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሏልና፤ “እኛ በተለያየን ጊዜ፣ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ታዛቢ ሆኖ ይቁም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ላባም “እንግዲህ ከዚህ በምንለያይበት ጊዜ እግዚአብሔር እኔንና አንተን ይጠብቀን” በማለት ያንኑ ስፍራ ምጽጳ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 ላባም አለው፥ “እኛ አን​ዳ​ችን ከሌ​ላው እን​ለ​ያ​ያ​ለ​ንና ራእ​ይን የገ​ለ​ጠ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ሆኖ ይመ​ል​ከት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 እኛ በተለያየን ጊዜ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይጠብቅ ብሎአልና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 31:49
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም የጌታ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ ተነሥቶም ገለዓድንና ምናሴን አቋርጦ ሄደ፤ ገለዓድ ባለችው በምጽጳ በኩል አድርጎም በአሞናውያን ላይ ዘመተባቸው።


አሞናውያን ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በገለዓድ በሰፈሩ ጊዜ፥ እስራኤላውያንም እንደዚሁ ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ።


ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! አድምጡ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ አሳ፥ ባዕሻ ራማን ለመመሸግ አከማችቶት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ከዚያ ለማንሣት እንዲረዳው ሕዝቡ አንድም ሳይቀር እንዲመጣ ወደ ይሁዳ ግዛቶች ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ንጉሥ አሳ ከዚያ የተገኘውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ወስዶ ምጽጳንና በብንያም ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የጌባዕን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራበት።


ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ አለቆች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም በላያቸው ላይ አለቃና አዛዥ አደረጉት፤ ዮፍታሔም የተናገረውን ቃል ሁሉ ምጽጳ ላይ በጌታ ፊት ደገመው።


አንተና እኔ ስለ ተነጋገርነው ነገር እነሆ፤ ጌታ በመካከላችን ለዘለዓለም ምስክር ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios