ላባም፥ “በዐይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና።
ዘፍጥረት 31:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሃያ አንድ ዓመት በጎችህንና ፍየሎችህን ስጠብቅ ኖርሁ፥ ከበጎችህም ጠቦቶችን አልበላሁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሃያ ዓመት ዐብሬህ ኖሬአለሁ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመንጋህ አንድ ጠቦት እንኳ አልበላሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሃያ ዓመታት ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም፥ የመንጎችህንም ጠቦቶች አልበላሁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንተ ጋር መኖር ከጀመርኩ ኻያ ዓመት ሆነኝ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ በጎችህና ፍየሎችህ የጨነገፉበት ጊዜ የለም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ በልቼ አላውቅም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሀያ ዓመት ሙሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም የመንጎችህንም ጠቦቶች አልበላሁም አውሬ የሰበረውን አላመጣሁልህም ነበር፤ |
ላባም፥ “በዐይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና።
ያዕቆብም አለው፥ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብቶችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታውቅምን? ጥቂት ሆነው አግኝቻቸዋለሁና፤
እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በሚፀንሱ ጊዜ ዐይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ዝንጕርጕሮችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።
አሁንም ዕቃዬን ሁሉ በረበርህ፤ ከቤትህስ ዕቃ ሁሉ ምን አገኘህ? እነርሱ በእኛ በሁለታችን መካከል ይፈርዱ ዘንድ በወንድሞችና በወንድሞችህ ፊት አቅርበው።