እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በሚፀንሱ ጊዜ ዐይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ዝንጕርጕሮችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።
ዘፍጥረት 31:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለኝ፦ ዐይንህን አቅንተህ እይ፤ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ሐመደ ክቦና ዝንጕርጕሮች ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን አይቻለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ‘መንጎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸው፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ቀና ብለህ ተመልከት፤ ላባ በአንተ ላይ የሚፈጽመውን ድርጊት ሁሉ አይቻለሁና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለኝ፥ ‘ዓይንህን አቅናና እይ፥ መንጋዎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት ፍየሎች ሁሉ ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉሮች እና ነቊጣ ናቸው፤ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፤ ላባ የፈጸመብህን በደል ስላየሁ ይህን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለኝ፦ ዓይንህን አቅንተህ እይ በበጎችን በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና። |
እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በሚፀንሱ ጊዜ ዐይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ዝንጕርጕሮችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።
የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሀት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መዋረዴንና የእጆችን ድካም አየ፤ ትናንትም ገሠጸህ።”
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠብቅሃልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በሀገሩ ድሃ ሲበደል፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ብታይ በሥራው አታድንቅ።
በግብፅ ያሉትን የወገኖችን መከራ ማየትን አይቻለሁ፤ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁ፤ አሁንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላክህ።’
እናንተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣችሁን እያበረዳችሁ፥ በደላቸውንም ይቅር እያላችሁ፥ ትክክለኛውን አድርጉላቸው፤ ፊት አይቶ የማያዳላ ጌታ በእነርሱና በእናንተ ላይ በሰማይ እንደ አለ ታውቃላችሁና።
ድሃ ነውና፥ ተስፋውም እርሱ ነውና ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮኽብህ፥ ኀጢአትም እንዳይሆንብህ ደመወዙን ፀሐይ ሳይገባ በቀኑ ስጠው።