ዘፍጥረት 31:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሕልም፦ ‘ያዕቆብ ያዕቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነሆኝ ምንድን ነው?’ አልሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መልአክ፣ ‘ያዕቆብ’ አለኝ፤ እኔም፣ ‘እነሆ አለሁኝ’ አልሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም፦ ያዕቆብ ሆይ አለኝ፥ እኔም፦ እነሆኝ አልሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያው ሕልም የእግዚአብሔር መልአክ ‘ያዕቆብ!’ ብሎ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆ፥ አለሁ!’ አልኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም፦ ያዕቆብ ሆይ አለኝ እኔም፦ እነሆኝ አልሁት። |
ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እንዲህ ሆነ። እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እንዲህም አለው፥ “አብርሃም! አብርሃም ሆይ፥” እርሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።
እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በሚፀንሱ ጊዜ ዐይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ዝንጕርጕሮችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።
ሐውልቱን ዘይት በቀባህባት፥ በዚያች ለእኔ ስእለት በተሳልህባት ሀገር የተገለጥሁልህ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወለድህባትም ምድር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ።”
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
እንዲህም አላቸው፥ “እነሆ፥ የአባታችሁ ፊት እንደ ዱሮ ከእኔ ጋር እንዳልሆነ አያለሁ፤ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው።
እግዚአብሔር እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደ መጣ በአየ ጊዜ እግዚአብሔር ከቍጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ፥ “ሙሴ! ሙሴ!” አለው እርሱም፥ “ይህ ምንድን ነው?” አለ።
ያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ፤ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ይልሃል። የዐመፅ እስራትን ከመካከልህ ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ማንጐራጐርንም ብትተው፥
እርሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ለእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራእይ እገለጥለታለሁ፤ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።
እግዚአብሔርም ደግሞ፥ “ሳሙኤል! ሳሙኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሥቶ ዳግመኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። እርሱም፥ “አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ” አለው።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንደ ገና ሦስተኛ ጊዜ ጠራው። እርሱም ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግዚአብሔር ልጁን እንደ ጠራው አስተዋለ።