Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 31:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ዐይ​ን​ህን አቅ​ን​ተህ እይ፤ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ሐመደ ክቦና ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮች ናቸው፤ ላባ በአ​ንተ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አይ​ቻ​ለ​ሁና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሱም ‘መንጎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸው፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ቀና ብለህ ተመልከት፤ ላባ በአንተ ላይ የሚፈጽመውን ድርጊት ሁሉ አይቻለሁና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሱም እንዲህ አለኝ፥ ‘ዓይንህን አቅናና እይ፥ መንጋዎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት ፍየሎች ሁሉ ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉሮች እና ነቊጣ ናቸው፤ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፤ ላባ የፈጸመብህን በደል ስላየሁ ይህን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እንዲህም አለኝ፦ ዓይንህን አቅንተህ እይ በበጎችን በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው፤ ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 31:12
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ያለ​ውን የሕ​ዝ​ቤን መከራ በእ​ው​ነት አየሁ፦ ከአ​ሠ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማሁ፤ ሥቃ​ያ​ቸ​ው​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤


ድሃ ነውና፥ ተስ​ፋ​ውም እርሱ ነውና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ጮ​ኽ​ብህ፥ ኀጢ​አ​ትም እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ደመ​ወ​ዙን ፀሐይ ሳይ​ገባ በቀኑ ስጠው።


የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም ፍር​ሀት ከእኔ ጋር ባይ​ሆ​ንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰ​ደ​ድ​ኸኝ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዋ​ረ​ዴ​ንና የእ​ጆ​ችን ድካም አየ፤ ትና​ን​ትም ገሠ​ጸህ።”


እና​ን​ተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣ​ች​ሁን እያ​በ​ረ​ዳ​ችሁ፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር እያ​ላ​ችሁ፥ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ ፊት አይቶ የማ​ያ​ዳላ ጌታ በእ​ነ​ር​ሱና በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ማይ እንደ አለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


በግ​ብፅ ያሉ​ትን የወ​ገ​ኖ​ችን መከራ ማየ​ትን አይ​ቻ​ለሁ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰም​ቻ​ለሁ፤ ላድ​ና​ቸ​ውም ወር​ጃ​ለሁ፤ አሁ​ንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላ​ክህ።’


ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠ​ብ​ቅ​ሃ​ልና፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላ​ሉና በሀ​ገሩ ድሃ ሲበ​ደል፥ ፍር​ድና ጽድ​ቅም ሲነ​ጠቅ ብታይ በሥ​ራው አታ​ድ​ንቅ።


ምላ​ሳ​ቸ​ውን እንደ እባብ ሳሉ፤ ከከ​ን​ፈ​ራ​ቸው በታች የእ​ባብ መርዝ አለ።


እኔ ግን በቸ​ር​ነ​ትህ ታመ​ንሁ፥ ልቤም በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ዋል።


“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ግፍ አታ​ድ​ርግ፤ አት​ቀ​ማ​ውም። የሞ​ያ​ተ​ኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ደ​ር​ብህ።


አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደረሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ውን ግፍ ደግሞ አየሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በጎቹ በሚ​ፀ​ንሱ ጊዜ ዐይ​ኔን አን​ሥቼ በሕ​ልም አየሁ፤ እነ​ሆም፥ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios