ዘፍጥረት 30:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም፥ “እኔ ብፅዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያም፣ “ምንኛ ደስተኛ ሆንሁ ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛዋ ይሉኛል” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ አወጣችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፥ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፥ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያም “እጅግ ደስ ብሎኛል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ሁሉ ‘ደስተኛዋ ሴት!’ ይሉኛል” ስትል ስሙን አሴር ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው። |
የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆችም፤ ጋድ፥ አሴር፤ እነዚህ በሁለቱ ወንዞች መካከል በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።
ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፤ ለእናቷ አንዲት ናት፥ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ ንግሥታትና ቁባቶችም አመሰገኑአት።