“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ዘፍጥረት 28:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከነዓናውያንም ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ፊት የተጠሉ እንደ ሆኑ ዔሳው በአየ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም የከነዓናውያን ሴቶች በአባቱ በይሥሐቅ ዘንድ የቱን ያህል የተጠሉ መሆናቸውን ተገነዘበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከነዓናውያንም ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ፊት የተጠሉ እንደ ሆኑ ዔሳው ባየ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም አባቱ ይስሐቅ የከነዓናውያንን ሴቶች እንደማይወድ ዔሳው ተገነዘበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከነዓናውያንም ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ፊት የተጠሉ እንደሆኑ ዔሳ ባየ ጊዜ፥ |
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”