አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
ዘፍጥረት 28:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፤ ተንተርሷት የነበረችውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆማት፥ በላይዋም ዘይትን አፈሰሰባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም በማግስቱም ማልዶ ተነሣ፣ ተንተርሶት ያደረውን ድንጋይ አንሥቶ እንደ ሐውልት አቆመው፤ በዐናቱም ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፥ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤ በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት። |
አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፤ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነሥቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ በሦስተኛውም ቀን ደረሰ።
ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፤ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና በዚያ አደረ፤ ከዚያም ስፍራ ድንጋዮች አንድ ድንጋይ አነሣ፤ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።
ሐውልቱን ዘይት በቀባህባት፥ በዚያች ለእኔ ስእለት በተሳልህባት ሀገር የተገለጥሁልህ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወለድህባትም ምድር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እኖራለሁ።”
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፤ ዘይትንም አፈሰሰበት።
አቤሴሎምም በሕይወቱ ሳለ፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” ብሎ ሐውልት ወስዶ በንጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ በስሙ አቁሞ ነበር፤ ያችም ሐውልት እስከ ዛሬ ድረስ “እደ አቤሴሎም” ተብላ ትጠራለች።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል አንዲቱ ከተማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ትሆናለች፤ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔርዐምድ ይሆናል።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ድንኳኑን ፈጽሞ በተከለባት፥ እርስዋንና ዕቃዋን ሁሉ በቀባና በቀደሰባት፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ በቀባና በቀደሰባት ቀን፥
ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።
ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በመሴፋና በአሮጌው ከተማ መካከል አኖረው፤ ስሙንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድኤት ማለት ነው።