La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 28:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕል​ምም አለመ፤ እነ​ሆም መሰ​ላል በም​ድር ላይ ተተ​ክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ይወ​ጡ​በ​ትና ይወ​ር​ዱ​በት ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሕልሙም፣ ጫፉ ሰማይ የሚደርስ መሰላል በምድር ላይ ቆሞ፣ በላዩም የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ አየ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕልምም አለመ፥ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርስ መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይወጡና ወደ ታች ይወርዱ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 28:12
24 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ በአ​ብ​ራም ድን​ጋጤ መጣ​በት፤ እነ​ሆም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ጽኑዕ ጨለማ መጣ​በት፤


በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”


ከሁ​ለት ዓመት በኋ​ላም ፈር​ዖን ሕል​ምን አየ፤ እነ​ሆም፥ በወ​ንዙ ዳር ቆሞ ነበር።


በደ​ድ​ሆ​ውም ዛፍ በታች ተኛ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አን​ቀ​ላፋ፤ እነ​ሆም፥ መል​አክ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።


እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።


ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብጽ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “በበ​ለስ ዛፍ ሥር አየ​ሁህ ስለ አል​ሁህ አመ​ን​ህን? ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ታያ​ለህ” አለው።


ከጥ​ንት ጀምሮ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ዐይ​ነ​ትና በብዙ ጎዳና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በነ​ቢ​ያት ተና​ገረ።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?