ዘፍጥረት 27:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ አባትህ ለወንድምህ ለዔሳው፦ እንዲህ ሲለው ሰማሁ፤ ‘ሂድና ከአደንኸው መብል አዘጋጅተህ አምጣልኝ፤ ሳልሞትም በልች በእግዚአብሔር ፊት ልባርክህ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ከመሞቴ በፊት በእግዚአብሔር ፊት እንድመርቅህ፣ ጥሩ ጣዕም ያለው ምግብ እንድበላ አዘጋጅልኝ።’ ሲለው ሰምቻለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘አደን አድነህ አምጣልኝ፥ ሳልሞትም በልቼ በጌታ ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል ሥራልኝ፤’ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሥራልኝ፤ ሳልሞትም በእግዚአብሔር ፊት እመርቅሃለሁ፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወንድምህ ለዔሳው፦ አደን አድነህ አምጣልኝ ሳልሞትም በልቼ በእግዚአብሔር ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል አድርግልኝ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ። |
በዚያችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረቷን በበኵር ልጁ የሚጥል፥ በሮችዋንም በታናሹ ልጁ የሚያቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።
እግዚአብሔርም ዛሬ በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ አልገደልኸኝምና ለእኔ መልካም እንዳደረግኽልኝ ለእኔ ነገርኸኝ።