Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 27:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ‘አደን አድነህ አምጣልኝ፥ ሳልሞትም በልቼ በጌታ ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል ሥራልኝ፤’ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ‘ከመሞቴ በፊት በእግዚአብሔር ፊት እንድመርቅህ፣ ጥሩ ጣዕም ያለው ምግብ እንድበላ አዘጋጅልኝ።’ ሲለው ሰምቻለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ‘አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሥራልኝ፤ ሳልሞትም በእግዚአብሔር ፊት እመርቅሃለሁ፤’

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “እነሆ፥ አባ​ትህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለዔ​ሳው፦ እን​ዲህ ሲለው ሰማሁ፤ ‘ሂድና ከአ​ደ​ን​ኸው መብል አዘ​ጋ​ጅ​ተህ አም​ጣ​ልኝ፤ ሳል​ሞ​ትም በልች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልባ​ር​ክህ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለወንድምህ ለዔሳው፦ አደን አድነህ አምጣልኝ ሳልሞትም በልቼ በእግዚአብሔር ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል አድርግልኝ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 27:7
7 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በጌታ ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ።”


ያደረግህልኝን በጎ ነገር ይኸው ነግረኸኛል፤ ጌታ እኔን በእጅህ ቢጥልልህም አንተ ግን አልገደልኸኝም።


የጌታ ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት የእስራኤልን ሕዝብ የባረከበት ቃለ ቡራኬ ይህ ነው።


ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።”


ርብቃም ልጇን ያዕቆብን እንዲህ አለችው፥ “እነሆ አባትህ ለወንድምህ ለዔሳው፦


አሁንም፥ ልጄ ሆይ፥ እኔ የማዝዝህ ነገር ስማኝ፥


ሄዶም አመጣ፥ ለእናቱም ሰጣት፥ እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios