እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
ዘፍጥረት 27:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናቱም አለችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያልሁህን አምጣልኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናቱም፣ “ልጄ ሆይ፤ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይድረስ፤ ግድ የለህም፤ እንደ ነገርሁህ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናቱም አለችው፦ “ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፥ ሂድና አምጣልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናቱም “ልጄ ሆይ፥ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደ ነገርኩህ አድርግ፤ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናቱም አለችው፦ ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን ቃሌን ብቻ ስማኝ ሂድና አምጣልኝ። |
እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
እኔ እዋሳለሁ፤ ከእጄ ትሻዋለህ፤ ወደ አንተ ባላመጣው፥ በፊትህም ባላቆመው፥ በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁህ ልሁን።
የቴቁሔዪቱም ሴት ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኀጢአቱ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን” አለችው።
በእግሩም ላይ ወደቀች፤ እንዲህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪያህ በጆሮህ ልናገር፥ የባሪያህንም ቃል አድምጥ።