ዘፍጥረት 26:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ ገብስ አገኘ፤ እግዚአብሔርም ባረከው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም በዚያች ምድር ዘር ዘራ፣ እግዚአብሔርም ባረከለትና በዚያ ዓመት መቶ ዕጥፍ አመረተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ፥ እግዚአብሔርም ባረከው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለ ባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ እግዚአብሔርም ባረከው። |
እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፤ አገነነውም፤ ላሞችንና በጎችን፥ ወርቅንና ብርን፥ ወንዶች ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን፥ ግመሎችንና አህዮችንም ሰጠው።
እንዲህም ሆነ፥ አብርሃምም ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን ባረከው፤ ይስሐቅም ዐዘቅተ ራእይ ተብሎ በሚጠራው ምንጭ አጠገብ ኖረ።
አምላክህ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር እንደ አለ በአየን ጊዜ በአንተና በእኛ መካከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እንዳታደርግ፤ እኛም በአንተ ላይ ክፉ እንዳናደርግ እንማማላለን።”
በዚህች ምድር ተቀመጥ፤ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህችን ምድር ሁሉ ለአንተም፥ ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህም ለአብርሃም የማልሁለትን መሐላ ከአንተ ጋር አጸናለሁ።
እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፤ መንጋዎቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩ።
እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤቱ ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኀይሉ ያወጣቸዋል፤ በመቃብር የሚኖሩ ኀዘንተኞችንም እንዲሁ።
ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንደ ሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።
ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።
በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል፤ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።”