Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፤ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሌላውም ዘር ደግሞ በመልካም መሬት ላይ ስለ ወደቀ በቅሎ አደገ፤ ፍሬም ሰጠ፤ አንዱ ሠላሳ፣ አንዱ ስድሳ፣ ሌላውም መቶ ፍሬ አፈራ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀ፤ አደገ፤ አድጎም ፍሬ ሰጠ፤ አንዱ ሠላሳ፥ አንዱ ስልሳ፥ አንዱም መቶ አፈራ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሌላው ዘር በመልካም መሬት ላይ ወድቆ በቀለ፤ ቡቃያውም አድጎ ፍሬ ሰጠ፤ አንዱ ሠላሳ፥ አንዱ ሥልሳ፥ አንዱም መቶ አፈራ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 4:8
21 Referencias Cruzadas  

እኔ የወ​ይን ግንድ ነኝ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም እና​ንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚ​ኖር እኔም በእ​ርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚ​ያ​ፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድ​ረግ አት​ች​ሉ​ምና።


ይህም ወደ እና​ንተ የደ​ረ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በእ​ው​ነት ከሰ​ማ​ች​ሁ​በ​ትና ከአ​ያ​ች​ሁ​በት ቀን ጀምሮ በመ​ላው ዓለም ያድ​ግና ያፈራ ዘንድ ነው።


በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው።”


ይስ​ሐ​ቅም በዚ​ያች ምድር ዘርን ዘራ፤ በዚ​ያች ዓመ​ትም መቶ እጥፍ ገብስ አገኘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው።


በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር።


ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ፤ አንዱም መቶ፥ አንዱም ስድሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።


በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ቅቅ መዶሻ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የጽ​ድ​ቅን ፍሬ ትሞሉ ዘንድ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤


ፈቃ​ዱን ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ወ​ድድ ግን ትም​ህ​ርቴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የም​ና​ገ​ረ​ውም ከራሴ እን​ዳ​ይ​ደለ እርሱ ያው​ቃል።


በመ​ል​ካም ምድር የወ​ደ​ቀው ግን ቃሉን በበ​ጎና በን​ጹሕ ልብ የሚ​ሰ​ሙና የሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ ታግ​ሠ​ውና ጨክ​ነ​ውም የሚ​ያ​ፈሩ ናቸው።


በመ​ል​ካም መሬት ላይ የወ​ደቀ ዘርም ነበረ፤ በበ​ቀ​ለም ጊዜ መቶ እጥፍ አፈራ።” ይህ​ንም ብሎ፥ “የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አላ​ቸው።


በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል፤ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።”


በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።


ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፤ እሾህም ወጣና አነቀው፤ ፍሬም አልሰጠም።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፤” አለ።


እር​ሱም ሕንጻ ሁሉ የሚ​ያ​ያ​ዝ​በት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤተ መቅ​ደስ ግንብ የሚ​ያ​ድ​ግ​በት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios