ዘፍጥረት 25:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም አብርሃም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ነው፤ አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን በዚያ ቀበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የዕርሻ ቦታ አብርሃም ከኬጢያውያን የገዛው ነበር፤ ከሚስቱ ከሣራ አጠገብ በዚያ ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእርሻው ቦታ አብርሃም ከሒታውያን ላይ የገዛው ነው፤ ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ ሣራ ጋር ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም አብርሃም ከሒታውያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ይህ ነው አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ። |
አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውንና ተቀባይነት ያለውን ግብዝ ያይደለ አራት መቶ ምዝምዝ ብር መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው።
በመምሬ ፊት ያለው ባለ ድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻም ለአብርሃም ጸና፤ እርሻው፥ በእርሱም ያለ ዋሻው፥ በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው ዕንጨት ሁሉ፤
በእርሻው ዳር ያለችውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን ይስጠኝ፤ መቃብሩ የእኔ ርስት እንዲሆን በሚገባው ዋጋ በመካከላችሁ ይስጠኝ፤ ከእርሱም እገዛለሁ።”
ከአባቶችም ጋር በአንቀላፋሁ ጊዜ ከግብፅ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ፤ በአባቶችም መቃብር ትቀብረኛለህ።” እርሱም፥ “እንደ ቃልህ አደርጋለሁ” አለ። እርሱም፥ “ማልልኝ” አለው።
አብርሃምንና ሚስቱ ሣራንም በዚያ ቀበሩአቸው፤ ይስሐቅንና ሚስቱ ርብቃንም በዚያ ቀበሩአቸው፤ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት