ዘፍጥረት 24:64 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርብቃም ዓይኖችዋን አቀናች፤ ይስሐቅንም አየች፤ ከግመልም ወረደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርብቃም እንደዚሁ አሻግራ ስትመለከት፣ ይሥሐቅን አየች፤ ከግመልም ወረደች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርብቃም ዐይኖችዋን አቀናች፥ ይስሐቅንም አየች፥ ከግመልም ወረደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርብቃ ይስሐቅን ባየች ጊዜ ከግመሏ ወረደችና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርብቃም ዓይኖችዋን አቀናች ይስሐቅንም አየች ከግመልም ወረድች። |
ሎሌውንም፥ “ሊቀበለን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማነው?” አለችው። ሎሌውም፥ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፤ እርስዋም ቀጸላዋን ወስዳ ተከናነበች።
እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ “አባቴን እርሻ ልለምነው” ብላ አማከረችው፤ እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።
እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ የእርሻ ቦታ ይሰጣት ዘንድ አባቷን እንድትለምነው ጎቶንያል መከራት። እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና አንጐራጐረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድደኸኛል” ብላም ጮኸች። ካሌብም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት።