ዘፍጥረት 24:61 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርብቃም ተነሣች፤ ደንገጥሮችዋም፥ በግመሎችዋ ላይ ተቀምጠው ከሰውዬው ጋር አብረው ሄዱ፤ ሎሌውም ርብቃን ተቀብሎ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ርብቃና አገልጋዮቿ ተዘጋጁ፤ ግመሎቻቸውም ላይ ወጥተው ሰውየውን ተከተሉት፤ በዚህ ሁኔታ አገልጋዩ ርብቃን ይዟት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርብቃም ተነሣች ደንገጥሮችዋም፥ በግመሎችም ላይ ተቀምጠው ያንን ሰው ተከተሉት፥ ሎሌውም ርብቃን ተቀብሎ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ርብቃ ከደንገጡሮችዋ ጋር ለመሄድ ተነሣች፤ በግመሎቹ ላይ ተቀምጠው ከአብርሃም አገልጋይ ጋር ለመሄድ ተዘጋጁ። በዚህ ዐይነት የአብርሃም አገልጋይ ርብቃን ይዞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርብቃም ተነሣች ደንገጥሮችዋም በግመሎችም ላይ ተቀምጠው ያንን ሰው ተከተሉት፤ ሎሌውም ርብቃን ተቀብሎ ሄደ። |
እኅታቸው ርብቃንም መረቁአትና፥ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላት ሀገሮችን ይውረስ” አሉአት።
ራሔልም የአባቷን ጣዖቶች ወስዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች፤ በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ፤ አንዳችም አላገኘም።
ምርኮውን ሲካፈል፥ በኀያላኑም ቸብቸቦ ላይ ወዳጆችን ሲወዳጅ ያገኙት አይደለምን? የሲሣራ ምርኮ በየኅብሩ ነበረ፤ የኅብሩም ቀለም የተለያየ ነበረ፤ የማረከውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአንገቱ ላይ ነበረ።
አቤግያም ፈጥና ተነሣች፤ በአህያም ላይ ተቀመጠች፤ አምስቱም ገረዶችዋ ተከተሉአት፤ የዳዊትንም መልእክተኞች ተከትላ ሄደች፤ ሚስትም ሆነችው።
ዳዊትም ሄዶ የአጥቢያ ኮከብ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግመኛም በማግሥቱ መታቸው፤ ከእነርሱም በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ጐልማሶች በቀር አንድም ያመለጠ የለም።