ዘፍጥረት 24:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬም ወደ ውኃው ጕድጓድ መጣሁ፤ እንዲህም አልሁ፥ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም ዛሬ ወደ ውሃው ጕድጓድ ስደርስ እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፤ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈቃድህ ቢሆን የመጣሁበትን ጕዳይ አቃናልኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬም ወደ ውኃው ምንጭ መጣሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጒድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ፤ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬም ወደ ውኃው ምንጭ መጣሁ እንዲህም አልሁ፦ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፤ |
እንዲህም አለ፥ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ለእኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብርሃም ወንድም ቤት መንገዴን አቀናልኝ።”
እርሱም አለው፥ “አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለምን አንተ በውጪ ቆመሃል? እኛም ቤትን፥ ለግመሎችህም ማደሪያን አዘጋጅተናል።”
ጌታውም እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።
በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን፥ ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾምን አወጅሁ።
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
እነርሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአይሁድም ወገኖች ሁሉ የተመሰከረለት ነው፤ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አንተን ወደ ቤቱ እንዲጠራህ የምታስተምረውንም እንዲሰማ አዝዞታል፤” አሉት።
ብላቴናውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፤ አሁንም ወደዚያ እንሂድ፤ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናልና” አለው።