ጉትቻውንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱንም የርብቃን ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፤ እነሆም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።
ዘፍጥረት 24:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለርብቃም ስሙ ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ጕድጓድ ወደ ሰውዬው ሮጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርብቃም ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱም ሰውየው ወዳለበት የውሃ ጕድጓድ ፈጥኖ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለርብቃም ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፥ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ምንጭ ወደ ሰውዬው ሮጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርብቃ ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱ የአብርሃም አገልጋይ ወዳለበት ውሃ ጒድጓድ እየሮጠ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለርብቃም ላባ የተባለ ወንድም ነበራት ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ምንጭ ወደ ሰውዮው ሮጠ |
ጉትቻውንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱንም የርብቃን ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፤ እነሆም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።
እኅታቸው ርብቃንም መረቁአትና፥ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላት ሀገሮችን ይውረስ” አሉአት።
ይስሐቅም ሚስት ትሆነው ዘንድ የሶርያዊውን የላባን እኅት፥ የሶርያዊውን የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ከሁለቱ ከሶርያ ወንዞች መካከል በወሰዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።
ተነሣና ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሂድ፤ ከዚያም ከእናትህ ከርብቃ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስትን አግባ።
ላባም የእኅቱን የርብቃን ልጅ የያዕቆብን ስም በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው።
እነርሱም፥ “እኛ ከካራን ነን” አሉት። “የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?” አላቸው። እነርሱም፥ “እናውቀዋለን” አሉት።