ዘፍጥረት 24:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናዪቱም ሮጠች፥ ለእናቷም ቤት ይህን ሁሉ ነገር ተናገረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጅቷ ሮጣ ሄዳ፣ የሆነውን ሁሉ ለእናቷ ቤተ ሰቦች ነገረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብላቴናይቱም ሮጠች፥ ለእናትዋም ቤት ይህን ነገር ሁሉ ተናገረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጅትዋ ወደ ቤት ሮጣ ሄደችና የሆነውን ሁሉ ለእናትዋና ከእርስዋ ጋር ላሉት ሁሉ ነገረቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናይቱም ሮጠች ለእናትዋም ቤት ይህን ነገር ሁሉ ተናገርች |
ይህንም ነገር ከአንደበቷ በሰማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰኘችኝ። ለጆሮዎችዋም ጉትቻዎችን ለእጆችዋም አምባሮችን አድርጌ አስጌጥኋት። ደስ ባሰኘችኝም ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።
ያዕቆብም የአባቷ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት፤ እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባቷ ይህን ነገር ነገረችው።
ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያም ድንኳን ገባና በረበረ፤ አላገኘምም፤ ከዚያም ወጣና ወደ ሁለቱ ዕቁባቶቹ ድንኳን ገባ፤ ነገር ግን አላገኘም። ወደ ራሔልም ድንኳን ገባ።