እንዲህም ሆነ፤ አብራም ወደ ግብፅ ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤
ዘፍጥረት 24:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማታውቅ ድንግል ነበረች። ወደ ውኃው ጕድጓድም ወረደች፤ ውኃም ቀዳች፤ እንስራዋንም ሞልታ ወጣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጃገረዲቱ እጅግ ውብና ወንድ ያላወቃት ድንግል ነበረች። ወደ ምንጩም ወርዳ ውሃ በእንስራዋ ሞልታ ተመለሰች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች፥ ወደ ምንጭም ወረደች እንስራዋንም ሞላች፥ ተመልሳም ወጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርብቃ ገና ወንድ ያልደረሰባት በጣም ቈንጆ ልጃገረድ ነበረች፤ እርስዋ ወደ ውሃው ጒድጓድ ወርዳ በእንስራዋ ውሃ ከቀዳች በኋላ ተመለሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች፤ ወደ ምንጭም ወረደች እንስራዋንም ሞላች ተመልሳም ወጣች። |
እንዲህም ሆነ፤ አብራም ወደ ግብፅ ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤
ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ በእጁ አስረከበው፤ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። ዮሴፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተዋበ ነበር።
እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወንድሜ ቃል ደጅ እየመታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።