ዘፍጥረት 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአራት መቶ ምዝምዝ ብር ዋጋ ምድር በእኔና በአንተ መካከል ምንድን ነው? እንግዲህ ሬሳህን በዚያ ቅበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታዬ ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋማ አራት መቶ ጥሬ ብር ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በአንተ መካከል ምን ቁም ነገር አለው? ይልቅስ ሬሳህን ቅበርበት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታዬ ሆይ፥ እኔን ስማኝ፥ የአራት መቶ ሰቅል ዋጋ መሬት በእኔና በአንተ መካከል ምንድነው? እንግዲህ ሬሳህን ቅበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጌታዬ የመሬቱ ዋጋ አራት መቶ ብር ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በእናንተ መካከል ምንድን ነው? ይልቅስ የሚስትህን አስከሬን እዚህ ቅበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የአራት መቶ ሰቅል ዋጋ ምድር በእኔና በአንተ መካክለ ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር። |
ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው።