የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ ዐወቁ፤ አፈሩም፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።
ዘፍጥረት 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዳምና ሚስቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ አይተፋፈሩም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩምም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳምና ሚስቱ ራቊታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አያፍሩም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ አይተፋፈሩም ነበር። |
የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ ዐወቁ፤ አፈሩም፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።
ጣዖታትን የሚቀርጹ ያንጊዜ አይኖሩም፤ የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩም ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ የማይረባቸውን የራሳቸውን ፍላጎት የሚያደርጉ ሁሉ ያፍራሉ።
ኀፍረትሽ ይገለጣል፤ ውርደትሽም ይታያል፤ ጽድቅ ከአንቺ ይወሰዳል፤ እንዲሁም በአንቺ ፋንታ ሰውን አሳልፌ አልሰጥም።
አታፍሪምና አትፍሪ፤ አቷረጂምና አትደንግጪ፤ የዘለዓለም እፍረትሽንም ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።
አቤቱ! የእስራኤል ተስፋ ሆይ! የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።
ርኩስ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ ውርደትንም አላወቁም፤ ስለዚህም ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ታላቆቹንና ታናሾቹን እኅቶችሽንም በተቀበልሽ ጊዜ መንገድሽን ታስቢያለሽ፤ ታፍሪማለሽ፤ ለአንቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰጣቸዋለሁ፤ ስለ ቃል ኪዳንሽ ግን አይደለም።
ብዙ መብል ትበላላችሁ፤ ትጠግቡማላችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።
በዚህም በዘማዊና በኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።
በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅ በክብሩ፥ በአባቱም ክብር፥ ቅዱሳንመላእክትን አስከትሎ ሲመጣ ያፍርበታል።