እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ጡብ እንሥራ፤ በእሳትም እንተኵሰው” ተባባሉ። ጡባቸውም እንደ ድንጋይ፥ ጭቃቸውም እንደ ዝፍት ሆነላቸው።
ዘፍጥረት 19:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነዪ፥ አባታችንን ወይን እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከርሱ ጋራ እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ዘር ከአባታችን እናትርፍ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነዪ አባታቻንንም የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ ጋር ተኝተን ከእርሱ ልጆች እንድናገኝ አባታችንን የወይን ጠጅ አጠጥተን እናስክረው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባታቻንንም የወይን ጠጅ እንጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ ከአባታችንም ዘር እንስቀር። |
እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ጡብ እንሥራ፤ በእሳትም እንተኵሰው” ተባባሉ። ጡባቸውም እንደ ድንጋይ፥ ጭቃቸውም እንደ ዝፍት ሆነላቸው።
በዚያችም ሌሊት አባታቸውን ወይን አጠጡት፤ ታላቂቱም ገባች፤ በዚያችም ሌሊት ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም፥ ስትነሣም አላወቀም።
“መምህር ሆይ! ሙሴ “የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሎ ጻፈልን።
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።