ዘፍጥረት 18:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋራ ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፥ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ተነጋግሮ ካበቃ በኋላ ከዚያ ስፍራ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ። |
እነዚያም ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ፤ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ።
እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ በገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፤ በዐይኖቹም የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከትመው አየ፤ የእግዚአብሔር መላእክትም ተገናኙት።