እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
ዘፍጥረት 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባርካታለሁና፥ ከአንተም ልጆችን እሰጣታለሁና፤ አሕዛብና የአሕዛብ ነገሥታት ከእርስዋ ይወጣሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ እባርካታለሁ ከርሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ የብዙም ሕዝቦች እናት ትሆን ዘንድ እባርካታለሁ፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ከርሷ ይወጣሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እባርካታለሁ፥ ደግሞም ከእርሷ ልጅ እሰጥሃለሁ፥ እባርካታለሁም፥ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፥ የአሕዛብ ነገሥታት ከእርሷ ይወጣሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋን እባርካታለሁ፤ ከእርስዋም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካታለሁ፤ የብዙ ሕዝቦችም እናት ትሆናለች፤ ከዘርዋም መካከል ነገሥታት የሚሆኑ ይገኛሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እባርካታለሁ፥ ደግሞም ከእርስዋ ልጅ እሰጥሃለሁ እባርካትማለሁ፥ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፤ የአሕዛብ ነገሥታት ከእርስዋ ይወጣሉ። |
እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ ቡሩክም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤
ያን ጊዜም የአግዚአብሔር ቃል ወደ አብራም እንዲህ ሲል መጣ፤ “እርሱ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚወጣው እርሱ ይወርስሃል።”
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለዘሩ አምላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
እኅታቸው ርብቃንም መረቁአትና፥ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላት ሀገሮችን ይውረስ” አሉአት።
እግዚአብሔርም አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማኅፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይወለዳሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።”
እግዚአብሔርም አለው፥ “አምላክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፤ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
ነገር ግን ከባሪያዪቱ የተወለደው ልደቱ ልዩ ነው፤ በሰው ልማድ ተወለደ፤ ከእመቤቲቱ የተወለደው ግን እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ተወለደ።
እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።