እግዚአብሔር አምላክም ለኖኅ አለው፥ “በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም ትውልድ የማደርገው የቃል ኪዳኔ ምልክት ይህ ነው፤
ዘፍጥረት 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውነታችሁን ቍልፈት ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፥ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆንል። |
እግዚአብሔር አምላክም ለኖኅ አለው፥ “በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘለዓለም ትውልድ የማደርገው የቃል ኪዳኔ ምልክት ይህ ነው፤
ዳዊትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ፥ “በመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን መልስልኝ” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።
የእግዚአብሔርን ፋሲካ ያደርግ ዘንድ ወደ እናንተ የመጣ መጻተኛ ቢኖር ወንዱን ሁሉ ትገርዛለህ፤ ያን ጊዜም ፋሲካ ያደርግ ዘንድ ይገባል፤ እንደ ሀገር ልጅም ይሆንላችኋል፤ ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ።
ሚስቱ ሲፓራም ባልጩት ወሰደች፤ የልጅዋንም ሸለፈት ገረዘች፤ “ይህ የልጄ የግርዛቱ ደም ስለ እርሱ ፈንታ ይሁን” ብላ ከእግሩ በታች ወደቀች።
የግዝረትንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚህም በኋላ ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛው ቀንም ገረዘው፤ እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን፥ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የቀደሙ አባቶችን ገረዙ።
ሳይገዘር እግዚአብሔር አብርሃምን በእምነት እንደ አጸደቀው በእርሱ ላይ ይታወቅ ዘንድ ግዝረትን የጽድቅ ማኅተም ትሆነው ዘንድ ምልክት አድርጎ ሰጠው። ሳይገዘሩ ለሚያምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብርሃም በእምነት እንደ ከበረ እነርሱም በእምነት እንደሚከብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው።