ዘፍጥረት 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአብራም ሚስት ሦራ ግን ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት አገልጋይም ነበረቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአብራም ሚስት ሦራ፣ ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤ እርሷም አጋር የምትባል ግብጻዊት አገልጋይ ነበረቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአብራም ሚስት ሦራ ግን ለአብራም ልጅ አልወለደችለትም ነበር፥ ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት ባርያም ነበረቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአብራም ሚስት ሣራይ ገና ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል አንዲት ግብጻዊት አገልጋይ ነበረቻት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአብራም ሚስት ሦራ ግን ለአብራም ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት ባሪያም ነበረቻት |
ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረጉለት፤ ለእርሱ በጎችም፥ በሬዎችም፥ አህዮችም፥ በቅሎዎችም፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም፥ ግመሎችም ነበሩት።
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ስለዚች አገልጋይህና ስለ ሕፃኑ አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና።
ይስሐቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ለመነ፤ መካን ነበረችና፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብቃም ፀነሰች።
እነሆ፥ ከዘመዶችሽ ወገን የምትሆን ኤልሣቤጥም እርስዋ እንኳ በእርጅናዋ ወንድ ልጅን ፀንሳለች፤ መካን ትባል የነበረችው ከፀነሰች እነሆ፥ ይህ ስድስተኛ ወር ነው።
ለሐናም ልጅ ስላልነበራት አንድ ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕልቃናም ከዚያችኛይቱ ይልቅ ሐናን ይወድድ ነበር። እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበር።