እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ወሰደለት፤ በየሁለትም ከፈላቸው፤ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልቈረጣቸውም።
ዘፍጥረት 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ ፀሐይም በገባ ጊዜ ነበልባል መጣ፤ የእሳት መብራትና የሚጤስ ምድጃም መጣ፤ በዚያም በተከፈለው መካከል አለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና ታየ፤ በተከፈለውም ሥጋ መካከል ዐለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፥ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፀሐይ ጠልቃ በጨለመ ጊዜ የምድጃ እሳት ጢስና ነበልባል ታየ፤ በተቈራረጠውም ሥጋ መካከል አለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ። |
እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ወሰደለት፤ በየሁለትም ከፈላቸው፤ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልቈረጣቸውም።
እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደች፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ እንጨቱንም፥ ድንጋዮቹንም በላች፤ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ፥ አፈሩንም ላሰች።
ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱንም መሥዋዕት አቀረበ፤ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት፤ እሳቱም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በላ።
እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጽመው ደነገጡ።
ሕዝቡም ሁሉ ነጐድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ሁሉ ፈርተው ርቀው ቆሙ።
ጽድቄ እንደ ብርሃን፥ ማዳኔም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም።
ከግብፅ ሀገር ከብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁትን፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ” ያልሁትን ቃሌን ስሙ።
ነበልባሉም ከመሠዊያዉ ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያዉ ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፤ በምድርም በግንባራቸው ወደቁ።
የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ ያለውን በትሩን ዘርግቶ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ አስነካ፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ በላች። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዐይኖቹ ተሰወረ።