ዘፍጥረት 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐሥራ አራተኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና ከርሱ ጋራ የተባበሩት ነገሥታት ወጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኤሚማውያን በሴዊ ቂርያታይም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፥ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አራተኛው ዓመት ከዶርላዖሜርና ከእርሱ ጋር የተባበሩት ነገሥታት ከነሠራዊቶቻቸው መጥተው ረፋያውያንን በዐስታሮት ቃርናይም፥ ዙዛውያንን በሃም፥ ኤማውያንን በሻዌ ቂርያታይም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይ፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፤ |
ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ወደ ቃሶን ወደ ዳዊት ወደ አዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በኀያላን ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
ብዙና እጅግ ያማረ መሰማርያም አገኙ፤ ምድሪቱም በፊታቸው ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ።
እንዳያጠፋቸው የቍጣውን መቅሠፍት ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ባጠፋቸው ነበር አለ።
አጫጅ የቆመውን እህል ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ ይሆናል፤ በሸለቆ እሸትን እንደሚሰበስብም እንዲሁ ይሆናል።
ስለ ሞአብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች፤ ተይዛማለች፤ መጠጊያዋም አፍራለች፤ ደንግጣማለች።
በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞሬዎናውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስጣሮትና በኤድራይን ተቀምጦ የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከገደሉት በኋላ፥
ከራፋይንም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።
ከገለዐድም የቀረውን የዐግን መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራፋይም ሀገር ተብላ ተቈጠረች።
ይኸውም እግዚአብሔር እንደ እናንተ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያም በኋላ ሁላችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።
በባሳን የነበረውን፥ በአስታሮትና በኤንድራይን የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ከረዓይት የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ አወጣቸው፤ ገደላቸውም።
በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስጣሮትና ኤድራይን ነበረ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች እኩሌታም በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞሬዎን ነገሥት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን፥ በአስታሮትና በኤድራይን በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።