ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረጉለት፤ ለእርሱ በጎችም፥ በሬዎችም፥ አህዮችም፥ በቅሎዎችም፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም፥ ግመሎችም ነበሩት።
ዘፍጥረት 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም በከብት፥ በብርና በወርቅ እጅግ በለጸገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ እጅግ በልጽጎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም ብዙ እንስሶች፥ ብዙ ብርና ወርቅ ያለው ሀብታም ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ። |
ለአብራምም ስለ እርስዋ መልካም አደረጉለት፤ ለእርሱ በጎችም፥ በሬዎችም፥ አህዮችም፥ በቅሎዎችም፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችም፥ ግመሎችም ነበሩት።
በአንድነትም ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም፤ ንብረታቸው ብዙ ነበርና፤ ስለዚህም ባንድነት ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቻቸውም።
እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፤ አገነነውም፤ ላሞችንና በጎችን፥ ወርቅንና ብርን፥ ወንዶች ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን፥ ግመሎችንና አህዮችንም ሰጠው።
ያዕቆብም እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ ሴቶችም ወንዶችም አገልጋዮች፥ ብዙ ከብትም፤ ላሞችም፥ በጎችም፥ ግመሎችና አህዮችም ሆኑለት።
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
ከብቶቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት፤ ሥራውም በምድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።
ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይልን ስለሚሰጥህ አምላክህን እግዚአብሔርን አስበው።
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።