ለምንስ ‘እኅቴ ናት’ አልህ? ለእኔ ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወስጃት ነበር። አሁንም እነኋት፥ ሚስትህ በፊትህ ናት፤ ይዘሃትም ሂድ።”
ዘፍጥረት 12:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ አብራም አዘዘ፤ እርሱንም፥ ሚስቱንም፥ የነበረውንም ሁሉ ሸኙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፈርዖን ስለ አብራም ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋራ አሰናበቱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ባዘዛቸው መሠረት ባለሟሎቹ አብራምንና ሚስቱን ካለው ሀብት ሁሉ ጋር ከአገር አስወጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ስዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው። |
ለምንስ ‘እኅቴ ናት’ አልህ? ለእኔ ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወስጃት ነበር። አሁንም እነኋት፥ ሚስትህ በፊትህ ናት፤ ይዘሃትም ሂድ።”