ዘፍጥረት 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቆአልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዪቱ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም እግዚአብሔር ሰዎቹን በምድር ሁሉ በተናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም፥ ጌታ በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደበላልቆ እነርሱንም ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በትኖአቸዋልና፥ ስምዋ ባቢሎን ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ እግዚአብሔር የሕዝቡን ቋንቋ ስለ ደበላለቀና እነርሱን በዓለም ዙሪያ ስለ በተናቸው የከተማውም ስም “ባቢሎን” ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። |
ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።
እርሱም በምድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖሩባትም ዘንድ ዘመንንና ቦታን ወስኖ ሠራላቸው።
ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቋንቋ ቢናገሩ፥ አላዋቂዎች፥ ወይም የማያምኑ ቢመጡ አብደዋል ይሉአቸው የለምን?