የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከእነዚህም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ ተዘሩ።
ዘፍጥረት 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዓለም ሁሉ ቋንቋ አንድ፥ ንግግሩም አንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩበትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ የዓለም ሕዝቦች መነጋገሪያ ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። |
የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከእነዚህም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ ተዘሩ።
እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፤ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ መሥራትን አይተዉም።
በዚያ ቀን አምስት የግብፅ ከተሞች በከነዓን ቋንቋ ይናገራሉ፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔርም ስም ይጠሩ ዘንድ ከተሞች አንድ ይሆናሉ፤ ከእነዚህም አንዲቱ የጽድቅ ከተማ ተብላ ትጠራለች።
ይህንም ቃል ሲናገሩ ሰምተው ሁሉም ደንግጠው ተሰበሰቡ፤ ሁሉም በየሀገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና የሚሉትን አጡ።