ዘፍጥረት 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራዲዎንን፥ ሰማርዮንን፥ አማቲንን ወለደ። ከዚህም በኋላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአራዴዎያውያን፣ የሰማሪናውያንና የአማቲያውያን አባት ነበረ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አርዋዳውያን፥ ጸማራውያን፥ ሐማታውያን ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የከነዓናውያን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አርዋዳውያን፥ ጸማራውያን፥ ሐማታውያን ነበሩ፤ ዘግይቶም የተለያዩት የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዐሩኬዎንንም፥ ሲኒንም፥ አራዴዎንንም፥ ሰማሪዎንንም፥ አማቲንም ወለደ። ከዚህም በኍላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ። |
የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን እስከ ጌራራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሴባዮም እስከ ላሳ ይደርሳል።
የአሦርም ንጉሥ ከባቢሎንና ከኩታ፥ ከአዋና ከሐማት፥ ከሴፌርዋይም ሰዎችን አመጣ፤ በእስራኤልም ልጆች ፋንታ በሰማርያ ከተሞች አኖራቸው፤ ሰማርያንም ወረሱአት፤ በከተሞችዋም ተቀመጡ።
እንደ ሔማት አርፋድ፥ እንደ አርፋድ ሴፋሩሔም፥ እንደ ሴፋሩሔም ካሌና፥ እንደ ካሌናም ደማስቆ፥ እንደ ደማስቆም ሰማርያ አይደለችምን?
አለቆችሽ በሲዶና ይኖሩ ነበር፤ የአራድ ሰዎችም ቀዛፊዎችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ! ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ፤ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ።