ዘፍጥረት 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሎሂምንና ቀፍቶሪምንም ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው፣ የከስሉሂማውያንና የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈትሮሳውያን፥ ከስሉሃውያን (ከእነርሱም ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው)፥ እና የካፍቶር ሕዝቦች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈትሮሳውያን፥ ከስሉሃውያን ሲሆኑ ከእነርሱም ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የካፍቶር ሕዝቦች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሉሂምን፥ ቀፍቶሪምንም ወለደ። |
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
በግብፅ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ፥ በሜምፎስም፥ በፋቱራም ሀገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦
ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮስንና ሲዶናን የቀሩትንም ረዳቶቻቸውን ታጠፋ ዘንድ ስለምትመጣው ቀን ነው፤ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንንና በከፍቶር ደሴት የቀሩትን ያጠፋልና።
“የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብፅ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከቀጰዶቅያ፥ ሶርያውያንንም ከጕድጓድ ያወጣሁ አይደለምን?
እስከ ጋዛም ድረስ በአሴሮት ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንንና ከቀጰዶቅያ የወጡ ቀጰዶቃውያንን አጠፉአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ ተቀመጡ።