ዘፍጥረት 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሦርም ከዚያች ሀገር ወጣ፤ ነነዌን፥ ረሆቦት የተባለችውን ከተማ ካለህን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ርኆቦትን፣ ካለህን መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ አሦር ሄደና ነነዌን፥ ረሆቦትን፥ ካላሕን መሠረተ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ወደ አሦር ሄደና ነነዌን፥ ረሖቦትን፥ ካላሕን መሠረተ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሦርም ከዚያች አገር ወጣ ነነዌን የረሆቦትን ከተማ፥ |
ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤቶች አለቆችም ቀርበው፥ “የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለአምላካችሁ እንሠዋለንና፥ እንደ እናንተም እንፈልገዋለንና ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው።
“አሦርና ሠራዊቱ ሁሉ በዚያ ተገደሉ፤ ሁሉም ድል ተነሡ፤ ወደ ጥልቅ ዐዘቅትም ጣሉአቸው ሠራዊቱም በመቃብር ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀው ተገደሉ።
ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ። እንዲህም በሉት፥ “ኀጢአትን ሁሉ አስወግድ፤ በቸርነትም ተቀበለን፤ በወይፈንም ፈንታ የከንፈራችንን ፍሬ ለአንተ እንሰጣለን።
የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ዳርቾቻችንንም በረገጠ ጊዜ እርሱ ይታደገናል።