ገላትያ 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሸክም ይሸከም፤ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእርስ በርሳችሁን ሸክም ተሸከሙ፥ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ እያንዳንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህ ዐይነት የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ። |
ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለም ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን የበደልን እስራት ፍታ፤ ጠማማውን ሁሉ አቅና፤ የተጨነቀውንም ሁሉ አድን፤ የዐመፃ ደብዳቤንም ተው።
እርሱም እንዲህ አለው፤ “ለእናንተ ለሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ! ሰውን ከባድ ሸክም ታሸክሙታላችሁ፤ እናንተ ግን ያን ሸክም በአንዲት ጣታችሁ እንኳን አትነኩትም።
“እርስ በርሳችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን ሕይወት የሚገኝበት የመንፈስ ሕግ እርሱ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶናልና።
የእግዚአብሔርን ሕግ የዘነጋሁ ሳልሆን፥ በክርስቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌላቸውን እጠቅማቸው ዘንድ ሕግ ለሌላቸው ሕግ እንደሌለው ሆንሁላቸው።
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።