ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ‘ትገዘሩ ዘንድና የኦሪትንም ሕግ ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል’ ብለው በነገር እንደ አወኩአችሁና ልባችሁን እንደ አናወጡት ሰምተናል።
ገላትያ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብሮኝ የነበረው ቲቶም አረማዊ ሲሆን እንዲገዘር ግድ አላልሁትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኔ ጋራ የነበረው ቲቶ እንኳ የግሪክ ሰው ቢሆንም፣ እንዲገረዝ አልተገደደም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከእኔ ጋር የነበረው ቲቶ እንኳ፥ ግሪካዊ ቢሆንም እንዲገረዝ አልተገደደም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኔ ጋር የነበረው ቲቶ ምንም እንኳ ግሪካዊ ቢሆን እንዲገረዝ አልተገደደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከእኔ ጋር የነበረ ቲቶ እንኳ የግሪክ ሰው ሲሆን ይገረዝ ዘንድ ግድ አላሉትም፤ |
ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ‘ትገዘሩ ዘንድና የኦሪትንም ሕግ ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል’ ብለው በነገር እንደ አወኩአችሁና ልባችሁን እንደ አናወጡት ሰምተናል።
ጳውሎስም ከእርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ፤ በዚያም ሀገር ስለ አሉት አይሁድ ወስዶ ገረዘው፤ አባቱ አረማዊ እንደ ነበረ ሁሉም ያውቁ ነበርና።
በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።