የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
ዕዝራ 8:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምርኮም የወጡት የምርኮኞች ልጆች ለእስራኤል አምላክ ለሚቃጠል መሥዋዕት ስለ እስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዘጠና ስድስትም አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባትም ጠቦቶች፥ ለኀጢአት መሥዋዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ። ይህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከምርኮ የተመለሱት፣ ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችን፣ ዘጠና ስድስት አውራ በጎችን፣ ሰባ ሰባት ተባዕት ጠቦቶችን፣ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኀጢአት መሥዋዕት ደግሞ ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎችን አቀረቡ። ይህም ሁሉ ለእግዚአብሔር የቀረበ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስር የመጡት ከምርኮ የተመለሱት ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ እስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶች፥ ለኃጢአት መሥዋዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ። ይህ ሁሉ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ቀጥሎ እነዚያ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን መባ ሁሉ አመጡ፤ በዚህ ዐይነት በመላው እስራኤል ሕዝብ ስም ዐሥራ ሁለት ኰርማዎችን፥ ዘጠና ስድስት የበግ አውራዎችንና ሰባ ሰባት የበግ ጠቦቶችን አቀረቡ፤ እንዲሁም ስለ ኃጢአታቸው ስርየት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ፤ እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምርኮም የወጡት ምርኮኞች ለእስራኤል አምላክ ለሚቃጠል መሥዋዕት ስለ እስራኤል ሁሉ አሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶችና ለኃጢአት መሥዋዕት አሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ። ይህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ። |
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
በዚህም በእግዚአብሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይፈኖችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም የበግ ጠቦቶች አቀረቡ፤ ስለ ኀጢአትም መሥዋዕት እንደ እስራኤል ነገዶች ቍጥር ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ።