ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ዕዝራ 7:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምላክህንም ሕግ፥ የንጉሡንም ሕግ በማያደርግ ሁሉ ላይ ሞት፥ ወይም ስደት፥ ወይም ገንዘብ መወረስ፥ ወይም ግዞት በፍጥነት ይፈረድበት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአምላክህ ሕግና ለንጉሡ ሕግ የማይታዘዝ ማንኛውም ሰው፣ የሞት ወይም የስደት ወይም የንብረት መወረስ ወይም የእስራት ቅጣት ይፈጸምበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአምላክህን ሕግና የንጉሡን ትእዛዝ በማያደርግ በማንም ላይ ሞት ወይም ስደት ወይም ንብረት መወረስ ወይም ግዞት በፅኑ ይፈረድበት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር ሕግ ወይም ለመንግሥት ሕግ ሁሉ የማይታዘዝ ማንም ሰው ቢኖር በጥንቃቄ እየተመረመረ በሞት ወይም ከሀገር በመባረር ወይም ሀብት ንብረቱን በመወረስ ወይም በእስራት ይቀጣ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምላክህንም ሕግ፥ የንጉሡንም ሕግ በማያደርግ ሁሉ ላይ ሞት ወይም ስደት ወይም ገንዘብን መወረስ ወይም ግዞት በፍጥነት ይፈረድበት።” |
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማይመጣ ሁሉ እንደ ሽማግሎችና እንዳለቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበዝበዝ፤ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስነገረ።
ይህንም ትእዛዝ የሚለውጥ ሁሉ ምሰሶው ከቤቱ ተነቅሎ እርሱ ይሰቀልበት፤ በላዩም ይገደል፤ ቤቱም የጕድፍ መጣያ ይደረግ ብዬ አዝዣለሁ።
ስሙ በዚያ የሚኖር አምላክ ይህን ይለውጡ ዘንድ፥ በኢየሩሳሌም ያለውንም የእግዚአብሔርን ቤት ያፈርሱት ዘንድ እጃቸውን የሚዘረጉትን ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ ያጥፋ። እኔ ዳርዮስ ይህን አዝዣለሁ፤ በትጋት ይፈጸም።”
እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ።