ዕዝራ 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በላይ ለማውጣት የሚያስፈልግህን ለአምላክህ ቤት የሚያሻውን ነገር ከንጉሡ ቤተ መዛግብት ስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በላይ ለአምላክህ ቤተ መቅደስ ለመስጠት የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ከንጉሡ ግምጃ ቤት መውሰድ ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በላይ ለአምላክህ ቤት የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ ከንጉሡ ቤተ መዛግብት ውሰድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤተ መቅደሱ መገልገያ የሚያስፈልግህንም ሌላውን ነገር ሁሉ ከቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ልትወስድ ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በላይ ለማውጣት የሚያስፈልግህን ለአምላክ ቤት የሚያሻውን ነገር ከንጉሡ ቤተ መዛግብት አውጣ። |