የይሁዳና የብንያምም ጠላቶች፥ የምርኮኞቹ ልጆች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መቅደስ እንደሚሠሩ ሰሙ።
ዕዝራ 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቁና ኀይለኛው አስናፍር ያፈለሳቸው፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶ ያኖራቸው፥ የቀሩትም አሕዛብ ደብዳቤውን ጻፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ታላቁና ኀያሉ አስናፈር አፍልሶ በሰማርያ ከተማና ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲሰፍሩ ካደረጋቸው ሌሎች ሕዝቦች ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቁና የተከበረው አስናፋር ያፈለሳቸው በሰማርያና በወንዝ ማዶ ያኖራቸው የቀሩትም አሕዛብ ደብዳቤውን ጻፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታላቁና ኀያሉ ንጉሠ ነገሥት አሰናፈር ከየተወለዱበት አገር በማዛወር በሰማርያ ከተማና ከኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል በየአውራጃው እንዲሰፍሩ ካደረጋቸው ከሌሎችም ሕዝቦች ጋር በመተባበር የተጻፈ ሲሆን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቁና ኃይለኛው አስናፈር ያፈለሳቸው፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶ ያኖራቸው እና የቀሩትም አሕዛብ ደብዳቤውን ጻፉ። |
የይሁዳና የብንያምም ጠላቶች፥ የምርኮኞቹ ልጆች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መቅደስ እንደሚሠሩ ሰሙ።
ንጉሡም ለአዛዡ ለሬሁም፥ ለጸሓፊውም ለሲምሳይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶም ለተቀመጡትና ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፥ “ከተማቸውን የሚሠሩ እነዚህ ደካሞች አይሁድ ኀይላቸው ምንድን ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን?” ብሎ ተናገረ።
“አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኀያል ጽኑዕና የተፈራኸው አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእኛና በነገሥታቶቻችን፥ በአለቆቻችንም፥ በካህናቶቻችንም፥ በነቢያቶቻችንም፥ በአባቶቻችንም፥ በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።
ለሁሉም እንደሚገባው አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ስጡ፤ ዐሥራት ለሚገባው ዐሥራትን ስጡ፤ ሊፈሩት የሚገባውን ፍሩ፤ ክብር የሚገባውንም አክብሩ።