የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ አናጢዎችንም፥ ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፤ ለዳዊትም ቤት ሠሩለት።
ዕዝራ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ብር ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ በባሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲዶናና ለጢሮስ ሰዎች መብልና መጠጥ፥ ዘይትም ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለድንጋይ ጠራቢዎችና ለየእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ገንዘብ ሰጡ፤ ከፋርስ ንጉሥ ከቂሮስ በተፈቀደው መሠረት የዝግባ ዛፎች ከሊባኖስ ወደ ኢዮጴ በባሕር እንዲያመጡላቸው፣ ለሲዶናና ለጢሮስ ሰዎችም ምግብ፣ መጠጥና ዘይት ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ገንዘብ ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ወደ ያፎ ባሕር እንዲያመጡ ለሲዶናውያንና ለጢሮሳውያን መብልና መጠጥ ዘይትም ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሕዝቡ ለግንበኞችና ለአናጢዎች የሚከፈለውን ገንዘብ ሰጡ፤ ከሊባኖስ ዛፍ ቈርጠው በኢዮጴ የባሕር ጠረፍ በኩል እንዲልኩላቸው ለጢሮስና ለሲዶና ከተሞች ነዋሪዎች ምግብን፥ መጠጥንና የወይራ ዘይትን ላኩ፤ ይህም ሁሉ የሆነው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ቂሮስ በሰጣቸው ፈቃድ መሠረት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጠራቢዎችና ለአናጢዎች ገንዘብ ሰጡ፤ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ በባሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲዶናና ለጢሮስ ሰዎች መብልና መጠጥ፥ ዘይትም ሰጡ። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ አናጢዎችንም፥ ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፤ ለዳዊትም ቤት ሠሩለት።
አሁንም ከወገኔ እንደ ሲዶናውያን እንጨት መቍረጥ የሚያውቅ እንደሌለ ታውቃለህና የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ይቈርጡልኝ ዘንድ አገልጋዮችህን እዘዝ፤ አገልጋዮቼም ከአገልጋዮችህ ጋር ይሁኑ፤ የአገልጋዮችህንም ዋጋ እንደ ተናገርኸው ሁሉ እሰጥሃለሁ።”
በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።
ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚመጣው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሆኑ የብር መዝጊያዎች፥ ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶችም፥ መለከቶችም፥ የወርቅና የብር ዕቃዎችም አልተሠሩም ነበር።
የእግዚአብሔርንም ቤት በሚሠሩት ላይ ለተሾሙት ሰጡ፤ እነርሱም ይጠግኑና ያድሱ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩ ሠራተኞች ሰጡአቸው።
በሰባተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ጀመሩ፤ የእግዚአብሔር መቅደስ ግን ገና አልተመሠረተም ነበር።
ይሁዳና እስራኤል ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ስንዴንም ይሸምቱልሽ ነበር፤ ሰሊሆትንና በለሶንን፥ ዘይትንና የተወደደ ማርን፥ ርጢንንም ከአንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።
ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ተቈጥቶ ነበር፤ በአንድነትም ወደ እርሱ መጥተው የንጉሡን ቢትወደድ በላስጦስን እንዲያስታርቃቸው ማለዱት፤ የሀገራቸው ምግብ ከንጉሥ ሄርድስ ነበርና።
በኢዮጴ ሀገርም ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ በትርጓሜውም ዶርቃስ ይሉአታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እርስዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽዋትም ትሰጥ ነበር።
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ነበርና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው ወደ እነርሱ መምጣት እንዳይዘገይ ይማልዱት ዘንድ ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።