ዕዝራ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዐቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለእያንዳንዱ ቀን እንደ ታዘዘው፣ በሚያስፈልገው ቍጥር ልክ የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ የዳስ በዓልን በተጻፈው መሠረት አከበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አከበሩ፤ እንደ ሥርዓቱም የዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በዕለቱ በቍጥር አቀረቡ፤ የዕለቱን ነገር በዕለቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕጉም በሚያዘው መሠረት የዳስ በዓልን አከበሩ፤ ለእያንዳንዱም ቀን የተመደበውን መሥዋዕት አቀረቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዓቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ። |
ከሦስትም ዓመት ወደ ላይ ላሉ በየሰሞናቸው ለሥራቸውና ለአገልግሎታቸው ዕለት ዕለት ወደ እግዚአብሔር ቤት ለሚገቡ ወንዶች ሁሉ፥
በፊቴ ባዶ እጅህን አትታይ። በእርሻም የምትዘራትን የፍሬህን በኵራት የመከር በዓል፥ ዓመቱም ሲያልቅ ፍሬህን ከእርሻ ባከማቸህ ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ።
“በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወትር በመሠዊያው ላይ ሁለት ንጹሓን የዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ።
“እነዚህንም፥ ከስእለታችሁና በፈቃዳችሁ ከምታመጡት ሌላ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእህልም፥ ለመጠጥም ቍርባን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕታችሁ በበዓላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።”
በኋለኛዪቱ በታላቅዋ የበዓል ቀንም ጌታችን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “የተጠማ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።