ሌዋውያኑም የኢዩኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳንን ልጅ ኢታንን፥
ዕዝራ 2:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዘምራኑ የአሳፍ ልጆች መቶ ሃያ ስምንት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዘምራኑ፦ የአሳፍ ዘሮች 128 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መዘምራኑ፦ የአሳፍ ልጆች፥ አንድ መቶ ሀያ ስምንት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ ሀያ ስምንት። |
ሌዋውያኑም የኢዩኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳንን ልጅ ኢታንን፥
የበረኞች ልጆች፥ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሰበዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
አናጢዎቹም የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠሩ ዘንድ መሠረት በጣሉ ጊዜ ካህናቱ ልብሳቸውን ለብሰው መለከቱን ይዘው፥ የአሳፍም ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው እንደ እስራኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት ሥርዐት እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ቆሙ።
በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚጀምሩ አለቃው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ ቦቂቦቅያ፥ የኢዶትም ልጅ፥ የጌላል ልጅ፥ የሰሙዓ ልጅ አብድያ።