የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
ሕዝቅኤል 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቃል በከለዳውያን ሀገር በኮቦር ወንዝ ላይ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባቢሎናውያን ምድር በኮቦር ወንዝ አጠገብ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቡዝ ልጅ፣ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ በዚያ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ቃል፥ በከለዳውያን አገር በኮቦር ወንዝ፥ ወደ ቡዚ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። በዚያም የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ሆነች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወሩም በአምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በከለዳውያን አገር በኮቦር ወንዝ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፥ |
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
በሠላሳኛው ዓመት በአራተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኮቦር ወንዝ በምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርንም ራእይ አየሁ።
መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ሆኖም አያያትም፤ በዚያም ይሞታል።
በቴልአቢብም ወደ አሉ፥ በኮቦርም ወንዝ አጠገብ ወደ ተቀመጡ ምርኮኞች መጣሁ፤ በተቀመጡበትም ቦታ ተቀመጥሁ፤ በዚያም በመካከላቸው እየተመላለስሁ ሰባት ቀን ተቀመጥሁ።
እኔም ተነሥቼ ወደ ሜዳው ሄድሁ፤ እነሆም በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ክብር ያለ የእግዚአብሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር፤ በግምባሬም ተደፋሁ።
ያመለጠውም ሳይመጣ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተች፤ ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም።
የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ፤ አጥንቶችም በሞሉበት ሸለቆ መካከል አኖረኝ።
በተማረክን በሃያ አምስተኛው ዓመት በዓመቱ መጀመሪያ ከወሩ በዐሥረኛው ቀን፥ ከተማዪቱ ከተመታች በኋላ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።
ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንደ አየሁት ራእይ ነበረ፤ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንደአየሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።
እንዲህም ሆነ፤ በስድስተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፥ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣ።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን በእስራኤልም ንጉሥ በኢዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥